Könyv የኢትዮጵያና የካናዳ አሳዳጆች ሳምሶን ኃ (ሳም ማርኤል)

የኢትዮጵያና የካናዳ አሳዳጆች

The Pursuers of Ethiopia and Canada

Nyelv: Afrikai
Kötés: Puha kötésű
Elérhetőség: Beszállítói készleten
Küldés 10-18 napon belül
11 176 Ft
የኢትዮጵያ እና የካናዳ አሳዳጆች፤በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ነገር ይዞ የመጣው መጽሐፍ፤ ምንስ አዲስ ነገር አለው?ያለወትሮው ብርዳማ የነበረው የቶሮንቶ ሰማይ...

Információk a könyvről

Nyelv
Afrikai
Kötés
Könyv - Puha kötésű
Kiadva
2026
oldal
444
EAN
9798197500717
Enbook ID
52746830
Súly
591
Méretek
152 x 229 x 23

Teljes leírás

የኢትዮጵያ እና የካናዳ አሳዳጆች፤
በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ነገር ይዞ የመጣው መጽሐፍ፤ ምንስ አዲስ ነገር አለው?
ያለወትሮው ብርዳማ የነበረው የቶሮንቶ ሰማይ፣ ዛሬ ደስ የሚል የፀሐይ ብርሃን ተተክቷል። ከተማዋ ፈገግ ብላለች፤ ነዋሪዎቿም በሰላማዊው ድባብ ተመስጠዋል። ነገር ግን ከዚህ ደማቅ ብርሃን በስተጀርባ፣ በከተማዋ ላይ የሚሰነዘር ከባድና አውዳሚ ሴራ እየተዶለተ ነው። መላ ነዋሪዎችንና ኢትዮጵያውያንንም ሊጠልፍ እየተሰናዳ ነው፡፡
ቶሮንቶ ወደ ምስቅልቅል ትርምስ ለመግባት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተዋታል። ይህንን አስከፊ ሴራ ግን ያቺ ብሩህ ፀሐይም ሆነች የፈገግታ ጭንብል የለበሰችው ከተማ ቅንጣት ያህል አያውቁም። መንግሥት፣ የደህንነት ተቋማትና ነዋሪዎች ከተማዋ ላይ ባለው በሰላማዊው ድባብ ተታለዋል። ከተማዋ ከበረዶ ሸሽታ በፀሐይ ስትደምቅ፣ ሳታውቀው በጉያዋ የታቀፈችው ጥፋት በድንገት በእሳት ብልጭታ ሊሞላት ነው!
ይህ ድንገተኛ አደጋ ባልታሰበ መንገድ ተጉዞ ከኢትዮጵያዊቷ ሕይወት ጋር እንዴት ሊተሳሰር ቻለ? እሷንስ በሴራው ወጥመድ ውስጥ ይጠልፋት ይሆን? ወይስ ሌላ የማይታሰብ ክስተት ይፈጠር ይሆን?
. . .
የመርማሪው ሄርሞን የመጨረሻ ተስፋ ሰላማዊ ዕረፍት ነበር-ነገር ግን ያገኘው ሳያስበው ሊገባ የደረሰው የሞት አፋፍ ላይ የሚያደርስ የሴራ ማዕበል ነው! በአሁኑ ሰዓት ግን እሱ ይሄንን አያውቅም። የሚያውቀው ነገር ቢኖር ላለፉት ዓመታት ያለ ዕረፍት ሲሠራ እንደነበር እና ዛሬ ስልኩን ዘግቶ ለሦስት ሳምንታት የሚቆይ የዓመት ዕረፍቱን በቶሮንቶው ሃይ ፓርክ (High Park) እንደጀመረ ብቻ ነው።
ነገር ግን በዛፎቹ ጥላ ስር የነበረው ጸጥታ በድንገት ተሰበረ። የሰማው ምስጢራዊ "ኮድ" ሁሉንም ነገር ቀየረው። ይህ ንግግርና ኮድ ለራሱም ወደ ሞት የሚወስደው፣ ለከተማዋም ውድቀትና መተራመስ ምክንያት የሚሆን ነው። ኢትዮጵያዊቷንም በስበት አውዳሚ ችግር ውስጥ የሚከት፣ በተጨማሪም አጠቃላይ የከተማ ነዋሪውንም ሆነ ከተማዋን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የሚከት ነው። ሰላምና ዕረፍት ፈልጎ የወጣው ሄርሞን፣ ባልታሰበ ሁኔታ በተለያዩ እሳቶች መሃል ወደቀ፦
የጊዜ ሩጫ፦

  • ያን ገዳይ ኮድ ለመፍታት ወደ አደገኛ መንገድ ሩጫውን ይጀምራል...
  • ማንም ሳያውቅ በሴራ የተወረረችውን ከተማ ለመታደግ ከአደገኛ ነገር ጋር ይጋጠማል...
  • የማይፈታውን ኮድ ለመፍታት ጥቂት ጊዜ ብቻ ሲቀሩት፣ ሄርሞን ከሞት ጋር ፊት ለፊት ይጋጠማል...
ለረዥም ጊዜ የተወሳሰበን ነገር ለመፍታት ያለው ጊዜ እጅግ አጭር ነው። ከባዱ ነገር ስለ ሴሬኞቹ ምንም አያውቅም፤ ይባስ ብሎ ደግሞ በዚህ ሴራ በደረሰበት አደጋ ራሱ ቆስሎ አቅም አጥቷል። በራሱ ሕመም