Könyv የአእምሮ ፈውስ በፍቅርተ ዋቅጅራ

የአእምሮ ፈውስ

እውነተኛ የሕይወት ምስክርነት

Nyelv: Amhar
Kötés: Puha kötésű
Elérhetőség: Várható készletfeltöltés
Küldés 30. 09. 2026
7 947 Ft
መግለጫታላቁና ሉዓላዊው አምላክ ተነግሮና ተዘክሮ የማያልቅ፣ ቢተረክ የማይሰለች ተአምራትን ሲሠራ ኖሯል፣ እየሠራም ይገኛል፣ ደግሞም ይቀጥላል። በዘላለማዊ እውቀ...

Információk a könyvről

Nyelv
Amhar
Kötés
Könyv - Puha kötésű
Kiadva
2026
oldal
108
EAN
9798182798211
Enbook ID
54032601
Súly
207
Méretek
152 x 229 x 7

Teljes leírás

መግለጫ

ታላቁና ሉዓላዊው አምላክ ተነግሮና ተዘክሮ የማያልቅ፣ ቢተረክ የማይሰለች ተአምራትን ሲሠራ ኖሯል፣ እየሠራም ይገኛል፣ ደግሞም ይቀጥላል። በዘላለማዊ እውቀቱና ችሎታው የብዙዎችን ታሪክ ቀይሯል፣ ደካሞችንና የሰይጣን እስረኞችን ከእስራት አላቋል፣ ኃጢአት ያሰቃያቸውንም ከኃጢአት እስራት ፈትቷል። በትንሿ አእምሮዬ ስንቱን ልተርክ? ብዙ ምሕረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ።

በሰው ልጆች ላይ ከሚከሰቱት ችግሮች መካከል አንዱ በሽታ ወይም ሕመም ተብሎ ይጠራል። አንዳንዶቹ በሽታዎች የሕክምና ሙያ ባላቸው ዘንድ በፍጥነት ለሞት የሚያደርሱ ተብለው ተመድበዋል፣ ለአብነትም የካንሰር በሽታ። በሌላ በኩል ደግሞ ቶሎ ባይገድሉም የዕድሜ ልክ ሕመም ወይም በሽታ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የጤና እክሎች መኖራቸው ይታወቃል። የዚህ መሰሉ ሰለባ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነበርኩ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎት በሽተኞችን መፈወስ እና በተለያየ መንገድ በአጋንንት እስራት ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ነፃ ማውጣት የተልዕኮው አንዱ ክፍል ነበር። ለዚህም ነበር እርሱ ራሱ ስለ በሽተኞች የታመመው እና በደዌ የደቀቀው (ኢሳ. 53፥4-5)።

ስለዚህም እውነተኛ የሕይወት ምስክርነቴን ለአንባቢዎቼ በማቅረብ፣ ለብዙዎች የጸሎት መልስ ሆና እንድትገለጥ የልቤ መሻትና ብርቱ ጸሎቴ ነው። መቼስ እዚህ ትደርሳለች ብሎ ያሰበ ሰው የለም፤ እኔም አስቤም አልሜም አላውቅም። የማዳንና ዕድሜ የመቀጠል ችሎታውና ልማዱ የሆነ ጌታ ኢየሱስ መለኮታዊ ፈውሱን ልኮ፣ በሰው ዘንድና በሕክምናው ዓለም ሐኪሞች እስኪደነቁ ድረስ የሚጠሩትን የአእምሮ ሕመም ፈውሶ፣ ይህን ምስክርነቴን በጽሑፍ ለማቅረብ አበቃኝ። ከዚያም አልፎ ለሌሎች በዚህ ሕመም ለሚሰቃዩት መፍትሔ አድርጎ ለክብሩ አቆመኝ።

ክብር ለፈዋሼና ለመድኃኒቴ ይሁን፤ አሜን። ሐዋርያው ዮሐንስ የቅዱሳን ምስክርነት የሚያስገኘውን ሌላ ድልና በረከት በሚመለከት ከሰማይ ድምፅ እንደሰማ ሁሉ፣ ይህ የሕይወት ምስክርነት ሰይጣንን ድል የሚያደርግ፣ ቅዱሳንን የሚያንፅ፣ እንዲሁም ታሪክ ሰሪውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያከብር በጽሑፍ ለማቅረብ በቃሁ። በጌታ ጸጋ ባሳለፍኩት ውጣ ውረዶች፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሆኑልኝ ድሎች ጸጋን የምትካፈሉበት እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ራሱን በዘመናት መካከል ያለ ምስክር የማይተው ጌታ ለእርሱና ለመንግሥቱ ሥራ ደቀ መዝሙር እሆንለት ዘንድ፣ በትውልዴ መካከል በእኔ የሠራውን የብርታቱን ጉልበት የገለጠበትን አስደናቂና እውነተኛ የሕይወት ምስክርነቴን እንካችሁ እላለሁ።